Fana: At a Speed of Life!

ዩ.ኤስ.ኤይድ በአፋር ክልል በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ650 ሺህ ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች የ650 ሺህ ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ድጋፉ ለህይወት አድን ስራዎች እንደሚውል ነው የገለጸው፡፡

እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችና በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች መጠለያ ማቅረብን እንደሚጨምር ነው የጠቀሱት፡፡

በተጨማሪም ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብና የጤና አጠባበቅና ንጽህናንም ያካትታል፡፡

ተራድኦ ድርጅቱ ለዚህም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር እንደሚሰራ ነው ያነሳው፡፡

ከአፋር ክልል በተጨማሪ በደቡብ፣ ኦሮምያ፣ሶማሌና ጋምቤላ ክልሎች በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.