Fana: At a Speed of Life!

ያልተለመደ አውሎ ነፋስ ወደ ታንዛኒያ እየተቃረበ መሆኑ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ያልተለመደ የተባለ አውሎ ነፋስ ወደ ታንዛኒያ እየተቃረበ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በማደጋስካር አቅራቢያ በደቡብ ሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ ጆቦ የተባለው ከባድ አውሎ ንፋስ ወደ ታንዛኒያ እየቀረበ መሆኑን የአየር ትንበያ ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡

አውሎ ነፋሱ ነፋስ ከቀላቀለና በሰዓት 100 ኪሎ ሜትር ከሚነፍስና ከባድ ማዕበል ጋር ተመጣጣኝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በታሪክ ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ በታንዛኒያ ዳርቻደረሱ ሁለት አውሎ ነፋሶች ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም በሃገሪቱ ከተከሰቱ አውሎ ነፋሶች አንጻር ሲታይ ጆቦ ደካማ የሚባል መሆኑንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ሆኖም አውሎ ነፋሱ በአህጉሪቱ ህዝብ በሚበዛባቸው ከተሞች የሚያልፍ ከመሆኑ አንጻር የሚያደርሰውን ጉዳት ከፍ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል፡፡

አውሎ ነፋሱ ከ6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ባሉባት ዳሬሰላም እና ዛንዚባርን ሊመታ ይችላልም ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.