Fana: At a Speed of Life!

ዮሚፍ ቀጀልቻ ሄንግሎ ላይ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሆላንድ ሄንግሎ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አሸነፈ፡፡

ዮሚፍ ርቀቱን 13 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ከ84 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቋል፡፡

እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሐሰን በ10 ሺህ ሜትር አሸንፋለች፡፡

ሲፈን ከዚህ ቀደም በፓውላ ራድክሊፍ ተይዞ የነበረውን የአውሮፓን የ10 ሺህ ሜትር ርቀት ክብረወሰንን አሻሽላለች፡፡

በዚህ ርቀት ሲፈንን በመከተል ኢትዮጵያዊቷ ፀሐይ ገመቹ ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.