Fana: At a Speed of Life!

ዮሲሂዴ ተሰናባቹን የጃፓን ገዢ ፓርቲ መሪ ሺንዞ አቤን በመተካት የፓርቲው መሪ በመሆን ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4 2013 (ኤፍ..) ዮሲሂዴ ሱገ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትርና የገዢው ፓርቲ መሪ ሺንዞ አቤን በመተካት የጃፓን ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ በመሆን ተመረጡ፡፡

ዮሲሂዴ ሱገ የፓርቲው መሪ ሆነው በመመረጣቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያደርጉትን ጎዞ ያቀልላቸዋል ተብሏል፡፡

71 ዓመቱ ዮሲሂዴ ዛሬ ይፋ በሆነው ምርጫ በቀላሉ ማሸነፋቸው ተነግሯል፡፡

በዚህም 534 ድምጽ ውስጥ 337 ድምጽ ማግኘታቸውን አልጀዚራ ዘገቧል።

ዮሲሂዴ ሱገ ተፎካካሪዎች የመከለከያ ሚኒስትሩ እና የቀድሞ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉምዮ ኪሺዳ እንደነበሩ ተሰምቷል፡፡

ረቡዕ በሚካሄደው ፓርላመንታዊ ምርጫ ከወዲሁ እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በህመም ምክንያት በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.