Fana: At a Speed of Life!

ዮሲሂዴ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በይፋ ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዮሲሂዴ ሱገ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በይፋ ተመረጡ፡፡

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሲሂዴ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤን በመተካት ነው የተመረጡት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑ የፓርቲያቸው ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው ምርጫ የ71 ዓመቱን ዮሲሂዴ ሱገ ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ መርጧል፡፡

ከሀገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት ከ 462 ድምጽ ውስጥ 314 ድምጽ ማግኘታቸው ነው የተሰማው፡፡

ከሺንዞ አቤ ጋር ቅርበት እንደነበራቸው የሚነገረው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፖሊሲያቸውን ያስቀጥላሉ ተብሏል፡፡

ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የመጨረሻ የካቢኔ ውይይታቸውን ዛሬ ያደረጉ ሲሆን በስልጣን ዘመናቸው ባበረከቷቸው ስኬቶች ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

 

ምንጭ፦ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.