Fana: At a Speed of Life!

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በተመረጡ የዓሣ ዝርያዎች ልማት ላይ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር በተጨማሪ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎቱን የበለጠ በማጠናከር በተመረጡ የዓሣ ዝርያዎች ልማት ላይ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በዓሣ እርባታ ላይ ከተሰማራው ከባቱ የዓሣ ሀብት ልማት ማዕከል ጋር በመተባበር በሽታ መቋቋም የሚችሉ የዓሣ ዝርያዎችን በማምጣት የዓሣ እርባታ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በዓሣ ልማት ዙሪያ ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.