Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች፡፡
ክትባቱ እድሜያቸው 60ና ከዛ በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስም 5 ሚሊየን ዜጎች ክትባቱን ያገኛሉ የተባለ ሲሆን ÷በዚህ ሳምንትም 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የጤና ባለሙያዎቸ ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር በአሁኑ ዙር የኤሌክትሮኒክ የክትባት መረጃ ስርዓትን በመጠቀም ረጅም ወረፋዎችን እያስቀሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እስከ አሁን በደቡብ አፍሪካ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ55 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በዚህም ሃገሪቱ በአፍሪካ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር በቀዳሚነት ላይ ትገኛለች፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.