Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ልታቋቁም ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤስ ኬ የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ የደን ልማት ኩባንያ ከደቡብ ኮሪያ የደን አገልግሎት ድርጅት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ሊያቀቋቁም መሆኑን አስታወቀ፡፡
 
ኩባንያው የቡና እርሻ ልማቱን በደቡብ ኢትዮጵያ የሚያቋቁም ሲሆን በስፍራው 10 ሺህ ስኩዌር ሜትር የሚሸፍን የደን ልማት እንዲሚያከናውን አስታውቋል፡፡
 
ለዚህም የአካባቢውን ስነ ምህዳር እንዲያገግም ለማድረግ እና ለመጠበቅ የሚረዳ 700 ሺህ ስኩዌር ሜትር ቦታ የሚሸፍን እጣንን ጨምሮ የተለያዩ የዛፍ ችግኞችን እንደሚተክልም ነው ያስታወቀው፡፡
 
ከቡና ልማቱ በተጨሪም በደን ልማት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሃገር ውስጥ ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡
 
በኩባንያው የሚለማው ቡና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለደቡብ ኮሪያ ገበያ ይቀርባልም ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- koreabizwire.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.