Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ እና ቻይና በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ፕሮግራም ዙሪያ ለመምከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ደቡብ ኮሪያና ቻይና በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ለመምከር መስማማታቸውን አስታወቁ፡፡

ይህ የተሰማው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ከቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

በውይይታቸው ወቅት የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ወደ ሲኦል በማቅናት ለሚያደርጉት ጉብኝት ሁኔታዎችን ለማመቻቸትም ተስማምተዋል፡፡፡

ፕሬዚዳንት ሙን ቻይና በቀጠናው ሰላምን ለማምጣት ለምታደርገው ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የቻይናው ባለስልጣን ወደ ጃፓን አቅንተው እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡

የእስያ ሃገራት የጆ ባይደንን መመረጥ ተከትሎ ሊኖር የሚችለውን አዲስ ግንኙነት በማስመልከት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተሸነፉት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ ከአቻቸው ኪም ጆንግ ኡን ጋር መቋጫ ያላገኙ ውይይቶችን ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.