Fana: At a Speed of Life!

“ዱን” የተሰኘው ፊልም የነገሠበት እና የዊል ስሚዝ ያልተጠበቀ ድርጊት የታየበት የኦስካር ሽልማት ትናንት ምሽት ተካሂዷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በሎስ አንጀለስ ዶልቢ ቴአትር በተካሄደው 94ኛው የኦስካር ሽልማት “ዱን” የተሰኘው ፊልም በስድስት ዘርፎች በማሸነፍ ቀዳሚ ሆኗል።
 
በኦስካር የሽልማት መርሃ-ግብር “ዱን” የተሰኘው ፊልም በአሥር ዘርፎች ሲታጭ ÷ በምርጥ ድምፅ፣ በምርጥ የፊልም ኤዲቲንግ እና በምርጥ ሲኒማቶግራፊ ዘርፎችን ጨምሮ በስድስት ዘርፎች በማሸነፍ ቀዳሚ ሆኗል።
 
በሽልማቱ “ኮዳ” የተሰኘው ፊልም በምርጥ ፒክቸር እና ምርጥ ረዳት ተዋናይን ጨምሮ በሦስት ዘርፎች አሸናፊ ሆኗል።
 
በአንፃሩ በ12 ዘርፎች በመታጨት ቀዳሚ የነበረው “ዘ ፓወር ኦፍ ዘ ዶግ” ፊልም በምርጥ ዳይሬክቲንግ ዘርፍ ጄን ቻምፒዮንን ብቻ ማስመረጥ ችሏል።
 
የምርጥ መሪ ተዋናይት ክብርን ጀሲካ ካስቲያን “ዘ አይስ ኦፍ ታሚ ፋይ” ላይ ባሳየችው የትወና ብቃት ስታሸንፍ የወንድ መሪ ተዋናይነቱን “ዊል ስሚዝ” በማሸነፍ የመጀመሪያ ኦስካሩን አሳክቷል።
 
ዊል ስሚዝ የሙያ አጋሩ የሆነው ክሪስ ሮክን ባልታሰበ ሁኔታ በጥፊ መማታቱም በመድረኩ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ እና የምሽቱ ያልተጠበቀ ድርጊት ሆኗል፡፡
 
ዊል ክሪስ ሮክን በጥፊ የመታው በባለቤቱ ጄዳ ፒንኬት ስሚዝ ፀጉር አቆራረጥ በመቀለዱ ነው ተብሏል።
 
የዊል ስሚዝ ባለቤት ለጸጉር መሳሳት በሚያጋልጥ ሕመም ተጠቂ መሆኗ ተዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.