Fana: At a Speed of Life!

በሃገሪቱ እየተካሔደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሃገሪቱ እየተካሔደ ያለውን የብልጽግና ጉዞ እና የለውጡን አመራሮች እንደሚደግፉ የሃረር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

ነዋሪዎቹ በከተማው በሚገኘው ኢማም አህመድ ስታዲየም በመገኘት የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ “በሀገሪቱ እየተከናወነ ያለውን የለውጥ ስራ እንደግፋለን”፣ “ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አመራር ጎን ነን” “ሃገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” እንዲሁም”ብልፅግና ለሁሉም ሁሉም ለብልፅግና” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ነው የድጋፍ ሰልፉን በሀረር ኢማም አህመድ ስታዲየም ያካሄዱት።

የሀረሪ ክልልና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን 20 ወረዳዎችና 4 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች  ነዋሪዎችም በድጋፍ ሰልፉ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድና ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸው ድጋፍ ለመግለፅ የተለያዩ የቁምና የጋማ ከብቶችን በመያዝ ” አባን ቢያ አቢይ ዳ ፓርቲን ኬኛስ በዳዲና”( መሪያችን ዐብይ ፓርቲያችን ብልፅግና) በማለት እየጨፈሩ ድጋፋቸውን ገልፀዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲ በድሪ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር በሃገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ከግቡ ለማድረስ ሁሉም ከብልፅግና ጎን ሊሰለፍ እንደሚገባ ገልፀው መንግስትም የህዝቡ የመልማት ፍላጎት ከግምት በማስገባት በትኩረት እንደሚሰራ ተሾመ ሀይሉ ዘግቧል።

በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማም በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ስራ በመደገፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

በከተማዋ ስታዲየም በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የከተማዋ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ሰልፈኞቹ የለውጡ አመራር ለሆኑት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉም በተለያዩ መፈክሮች ገልፀዋል።

ዱከምም በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ስራ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ ተካሂዷል።

ሰልፈኞቹ “በሀገሪቱ እየተከናወነ ያለውን የለውጥ ስራ እንደግፋለን”፣ “ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አመራር ጎን ነን”  የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ነው የድጋፍ ሰልፉን ያካሄዱት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.