Fana: At a Speed of Life!

ዲያጎ ማራዶና በ60 አመቱ ህይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው አንጋፋ የእግር ኳስ ተጫዋች ዲያጎ ማራዶና በ60 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ተሰማ።
በዓለም ላይ በድንቅ የእግር ኳስ ብቃቱ እና ብዙም ስኬታማ ባልነበረበት አሰልጣኝነት የሚታወቀው ዲያጎ ማራዶና በልብ ህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
ማራዶና በድንገተኛ የልብ ህመም በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ህይወቱ አልፏል ተብሏል።
በቅርቡ ከአንጎል የደም መርጋት ህመም ጋር ተያይዞ ስኬታም የቀዶ ህክምና ያደረገው ማራዶና ከአልኮል ሱሰኝነት ለመውጣት ህክምና ማግኘት ይጠበቅበት እንደነበረ ዘገባው አመልክቷል።
የሁልጊዜም የአለም ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ዲያጎ ማራዶና በፈረንጆቹ 1986 የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና ስታነሳ የቡድኑ አንበል ነበር።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.