Fana: At a Speed of Life!

ዲጂታል የድርቅ አዝማሚያ ክትትል እና ትንበያ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዲጂታል የድርቅ አዝማሚያ ክትትል እና ትንበያ መሳሪያ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የዝናብ አመጣጥ መጠን፣ ቆይታ እና ስርጭት በልማት ሥራ ላይ የሚኖረውን ተፅእኖ ለመቀነስ የሚያስችሉ ምርምሮችን ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህም የአየር ሁኔታ፥ ፀባይ እና በድርቅ ላይ ለአርሶ አደሩ የሚሆን መረጃ ተደራሽ ለማድረግ እና ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚረዳ አዲስ የድርቅ ክትትል እና ትንበያ ዘመናዊ መሳሪያ ገንብቷል።

ቴክኖሎጂው ለግብርና ኤክስቴንሽን ዘርፍ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቢሆንም በተጨማሪነት ለተፈጥሮ አደጋ ቅነሳ እና ለምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ተቋማትም ተመሳሳይ አገልግሎት መስጠት የሚችል መሆኑ ተነስቷል።

ይሄው የድርቅ ክትትል እና ትንበያ ስርዓት የሚመለከታቸው የመንግስት ኃላፊዎች የዘርፉ ተመራማሪዎች እና የግብርና ባለሙያዎች በተገኙበት ምክክር እየተካሄደበት ነው፣ አገልግሎቱን የማስመረቅ ስነ ስርዓትም ይካሄዳል።

አዲሱ ቴክኖሎጂ በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ድርቅ እና ከግብርናው ጋር ለተያያዙ የክትትልና ትንበያ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

በተለይም አርሶ አደሩ ራሱን አስማምቶ ችግሩን እንዲቋቋም መንግስትም ለውሳኔ የሚረዳው እንደሆነ ነው የተገለፀው።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.