Fana: At a Speed of Life!

ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ስኬት እየተመዘገበባቸው ነው-አምባሳደር ዲና ሙፍቲ 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ የሚደርሰውን የውጭ ጫና ለመከላከል የሚደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ስኬት እየተመዘገበባቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ ያልተገባ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እያደረጉ ነው።

በተለይም ሰሜኑ የአገሪቱ አካባቢ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ ወደ ትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት እውቅና የመንፈግ አካሄድ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን ለማጣራትና የድርጊቱ ፈጻሚ አካላት ላይ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያደርገውንም ጥረት ከቁብ ያለመቁጠር ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የዓለም የጸጥታ ስጋት አስመስሎ በማቅረብ የታችኛው ተፋሰስ አገራት በመንግስታቱ ደርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ጉዳዩ እንዲያልቅ የሚያደርጉትን ጥረትም ሌላኛው ጫና መሆኑን ገልጸዋል።

ጎን ለጎንም የሱዳን መንግሥት በሕገ-ወጥ መልኩ የኢትዮጵያን መሬት መያዙንና ይህም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና የብሔራዊ ጥቅሟን የሚገዳደር የውጭ ጫና መሆኑንም ነው የተናገሩት።

እነዚህን ወቅታዊ ጉዳዮችን ተንተርሶ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉትን ያልተገቡ ጫናዎች ለመከላከልና ለመቋቋም የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውን አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.