Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዳያስፖራው እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡
 
የኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ፒስ ኤንድ ፕሮግረስ ምክትል ፕሬዚደንት እና የአባይ ንጉሶች የሚዲያ መስራች ኡስታዝ ጀማል በሽር አህመድ ÷በዓረቡ ዓለም ስለ ህዳሴው ግድብ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለማስተካከል ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
እስካሁን በተደረጉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች እና የተለያዩ በዓረብኛ ቋንቋ የተሰሩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ኤርትራዊያን ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን አንስተዋል፡፡
 
ሌሎችም በቋንቋው መናገር የሚችሉ አጋሮችም ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡
 
ኡስታዝ ጀማል በቅርቡ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ በበድር ኢትዮጵያ እንዲሰበሰብ ያስተባበሩ ሲሆን÷ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ስለ ሀገራቸው እና ህዳሴው ግድብ በመሟገትም ይታወቃሉ፡፡
 
የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሃይሉ አብረሃም በበኩላቸው÷ዳያስፖራው በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች፣ በትልልቅ ሚዲያዎች እና በሰላማዊ ሰልፎች ጭምር በተለያዩ ከተሞች ድምጹን እያሰማ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
 
ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ከ15 ቢሊየን ብር በላይ ማዋጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
በአባይ ዙሪያ ለዘመናት ሲሰራ የነበረውን የሀሰት ትርክት የማረም ዲፒሎማሲያዊ ስራም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡
 
በአፈወርቅ አለሙ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.