Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ አገራቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የወደ አገር ቤት ጥሪን ተቀብለው አዲስ አበባ የገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ አገራቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ዲያስፖራዎቹ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ጋር መክረዋል።
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሰለሞን ነጋሽ፣ በአትላንታ የኢንፎርሜሽን ሲስተም አርክቴክቸር ባለሙያ አህመድ ጀማል እና በቨርጂኒያ የመረጃ እና የመሰረተ ልማት ደህኅነነት አማካሪ ፍስሃ ደስታ አገራቸውን በዘርፉ ለማገልገል እንደሚፈጉ ገልጸዋል።
የዲጂታል አግልግሎቶች ጥራት እና ደረጃን በማስጠበቅ፣ በዲጂታል ሴኩሪቲ፣ በዲጂታል ኦዲትና በዲጂታል ኢኖቬሽን ላይ ያላችውን እውቀት ለማካፍል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በዘርፉ የተሰማሩና በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎችን በማስተባበር ድጋፍ እናደርጋለን ማለታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ዲያስፖራዎቹ አገራቸውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በመምጣታቸው አመስግነው፥ ስለኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ገለፃ ማድረጋቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.