Fana: At a Speed of Life!

ዴሞክራሲ በአሜሪካ ቁልቁል እየተንሸራተተ መሆኑን ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይናው ሬንሚን ዩኒቨርሲቲ ቾንግ ያንግ የምጣኔ ሐብት ጥናቶች ኢኒስቲትዩት “ለአሜሪካ ዴሞክራሲ 10 ጥያቄዎች ” በሚል ርዕስ የሠራውን ጥናት ይፋ አደረገ፡፡

እንደ ኢንስቲትዩቱ አሜሪካ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዴሞክራሲን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመሸፈን እና አሜሪካውያንን ለመበታተን እንደ መሣሪያ ተጠቅማበታለች ብሏል፡፡

በውጪ ደግሞ አሜሪካ የበላይነቷን ለማስቀጠል የዓለም አቀፉን ሥርዓት በመደፍጠጥ በአገራት የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ዴሞክራሲን እያኮሰሰች መሆኗንም ጥናቱ አመላክቷል፡፡

በጄኔቫ ዲፕሎማሲ ትምህርት ቤት የዓለም አቀፍ ህግ ፕሮፌሰር የሆኑት አልፍሬድ ዲ ዛያስ በበኩላቸው፥ የተሳሳተ ዜና፣ የተሳሳተ ታሪክ፣ የተሳሳተ ዲፕሎማሲ ተቀባይነት ባገኘበት ዓለም የተጭበረበረ ዴሞክራሲን ማየት አያስደንቅም ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ በፈረንጆቹ ሕዳር 22 መቀመጫውን ስቶኮልም ያደረገው ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ እና ምርጫ ድጋፍ ኢንስቲትዩት ያወጣው ሪፖርት የአሜሪካን የዴሞክራሲ አተገባበር “ቁልቁል እየተንሸራተተ ያለ” ዴሞክራሲ ነው ሲል መግለጹን ደግፈው፥ አሜሪካ መጀመሪያም ቢሆን እንደሚባልላት መቼ የ ”ዓለም አቀፍ ዴሞክራሲ መሠረት” ነበረች ሲሉ ጠይቀዋል።

አሜሪካውያን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት አላቸው፤ የፈለጉትን አመለካከትም ማንጸባረቅ ይችላሉም ነው ያሉት።

ነገር ግን ከተጻፈው ዴሞክራሲያዊ መብታቸው በተቃራኒ የአገሪቷ መንግስት እና የግል መገናኛ ብዙኃን በተቀናጀ መልኩ ማኅበረሰቡን እውነት በሚመስል የሃሰት መረጃ በተደጋጋሚ አጭበርብረዋል ሲሉም የዓለም አቀፍ ህግ ፕሮፌሰሩ አልፍሬድ ዲ ዛያስ ይናገራሉ፡፡

በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሂስ በመስጠት የሚታወቁት ኖአም ቾምስኪም፥ “እያደገ ከሚገኘው ዴሞክራሲ በተቃራኒው “ኒው ዮርክ ታይምስን” እና “ዋሽንግተን ፖስት”ን ጨምሮ በአሜሪካ የሚሰሩ መገናኛ ብዙኃን ውሸት እያመረቱ እያከፋፈሉ ነው” ሲሉ የአሜሪካ ዴሞክራሲ በትክክለኛ መንገድ ላይ እየተጓዘ እንዳልሆነ መግለጻቸውን የሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.