Fana: At a Speed of Life!

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ክትባት ልትሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ክትባት ለዜጎቿ ልትሰጥ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በሃገሪቱ ሰሜናዊ ኪቩ ግዛት ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸውን ተከትሎ በምስራቃዊ ኮንጎ ክትባት መስጠት ሊጀመር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሃገሪቱ የ42 ዓመት እና የ60 ዓመት ሴት በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች ክትባቱ መሰጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡

በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ከተዳረጉት የመጀመሪያ ሴት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 161 ሰዎች በአካባቢው መገኘታቸውም ተሰምቷል፡፡

ቫይረሱ አዲስ የኢቦላ ዝርያ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ በመዲናዋ ኪንሻሳ ናሙናዎች ተወስደው ጥናት እየተደረገባቸው ነው፡፡

የመጨረሻውና የብዙ ሰዎችን ህይዎት የቀጠፈው በምስራቃዊ የሃገሪቱ ክፍል ሲሆን ይህም በፈረንጆቹ 2018 እና 2020 ነበር፡፡

በዚህም ቫይረሱ 2ሺህ 287 ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.