Fana: At a Speed of Life!

ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ 25 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎትድርጅት በ2012 በጀት ዓመት 25 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የ2012 በጀት ዓመት በተለይ የአፈር ማዳበሪያና ስንዴን የማጓጓዝ ስራ በመሰራቱ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበትና ስኬታማ የሆነበት ዓመት መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት ዓመት 46 መርከቦችን በማሰማራት ከ24 ሚሊየን ኩንታል በላይ የዳቦ ስንዴና የአፈር ማዳበሪያን ማጓጓዙንና በስኬት ማጠናቀቁን አቶ ሮባ መገርሳ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በባሕር ትራንስፖርት፣ በደረቅ ወደብ፣ በየብስ ትራንስፖርት እንዲሁም በመልቲሞዳል የኦፕሬሽን ስራዎች አገልግሎት አጠቃላይ 11 ሚሊየን ቶን ገቢ እና ወጪ ጭነት ማስተናገድ ተችሏል ነው የተባለው፡፡

ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ከተስተናገደው 7 ሚሊየን ቶን ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበና የ37 በመቶ ጭማሪ ያሳየ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሌላው የበጀት ዓመቱ ስኬት ከዚህ በፊት ከ700 ሺህ ቶን ያልበለጠ ጭነት የሚሰሩት የድርጅቱ መርከቦች ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ሚሊየን ቶን በላይ ጭነት ማጓጓዝ መቻላቸው እንደሆነም ተጠቁሟል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.