Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የሰጡት አስተያየት ከእርሳቸው የማይጠበቅ ነው – ሴናተር ጄሰን ክሮው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ሴናተር ጄሰን ክሮው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያደረጉትን ንግግር ተቃወሙ፡፡

የኮሎራዶው ሴናተር በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የፕሬዚዳንት ትራምፕ “ግብፅ የህዳሴ ግድብን ልታጋይ ትችላለች” ንግግር ከእርሳቸው የማይጠበቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ንግግር የግድቡን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከግንዛቤ ያላስገባ ነውም ብለዋል፡፡

ሴናተሩ ኢትዮጵያ የአሜሪካ የረዥም ዘመናት የልብ ወዳጅ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

አሜሪካ ስለ ህዳሴው ግድብ አደራዳሪ እንጂ የአድልዎ ጣልቃ ገብነት አያስፈልጋምም ነው ያሉት፡፡

ጉዳዩ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲያልቅ መስራት እንጂ፤ እርዳታን እናቋርጣለን በሚል ማስፈራሪያ መሸበብ የለበትም ሲሉም የትራምፕን ንግግር ተቃውመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.