Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ጄኔራል ሞተርስ የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት አዘዙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኪና አምራቹ ጄኔራል ሞተርስ የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት አዘዙ።

ፕሬዚዳንቱ ጄኔራል ሞተርስ ለኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች የሚያገለግል የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት ነው ትዕዛዝ ያስተላለፉት።

“ጄኔራል ሞተርስ ጊዜ እያባከነ ነው ያሉት” ትራምፕ የኩባንያውን ዋና ስራ አስፈጻሚ በነገር ሸንቁጠዋቸዋልም ነው የተባለው።

የአሁኑን ትዕዛዝ ፕሬዚዳንታዊ የማስገደድ ስልጣን የሰጣቸውንና በኮሪያ ጦርነት ወቅት የወጣውን ለመከላከያ አገልግሎት የሚውሉ ምርቶችን ማምረት የሚመለከተውን ደንብ ጠቅሰው ያስተላለፉት ነው ተብሏል።

እርምጃው አሜሪካውያንን ከከኮሮና ቫይረስ ለመታደግ የተወሰደ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ የገለጹት።

በአሜሪካ የመተንፈሻ አካላትን በሚያጠቃው የኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ለመታደግ የሚያገለግለው የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እጥረት መኖሩ ይነገራል።

ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኩባንያዎችና ሃገራት ይህን መሳሪያ እያመርቱና እንዲያቀርቡ ጠይቀው ነበር።

ጄኔራል ሞተርስ በበኩሉ ከቀጣዩ ሚያዚያ ወር ጀምሮ በየወሩ 10 ሺህ ቬንትሌተሮችን አመርታለሁ ማለቱ ይታወሳል።

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ 104 ሺህ ሰዎች ሲያዙ፥ ወደ 1 ሺህ 700 የሚጠጉት ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በአንጻሩ ጣሊያን እና ስፔን በኮሮና ቫይረስ በአንድ ቀን ከፍተኛውን የሞት ቁጥር አስመዝግበዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.