Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ሊያ ሰብዓዊ እርዳታን በተመለከተ በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊዩ ታደሰ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ክላውዴ ጂቢዳር ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ በግጭት እና በድርቅ ምክንያተ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በሚደረጉ የሰብዓዊ እርዳታዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡
 
በተጨማሪም ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ለማዳረስ የሚከናወነውን ስራ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.