Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ሊያ ከኳታር የህብረተሰብ ጤና ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከኳታር የህብረተሰብ ጤና ሚኒስትር ጋር ተወያዩ፡፡

ሁለቱ ሚኒስትሮች በውይይታቸው በጤናው ዘርፍ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የስምምነቱ አላማ በሀገራቱ መካከል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አጠባበቅ ስርዓት ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የጤና መረጃ ስርዓቶችን፣ የጤና ባለሙያ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ፣ እንዲሁም በጤና ዙሪያ የሚደረጉ ምርምሮች እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ዶክተር ሊያ በፌስቡለክ ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.