Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ከኖርዌይ አቻቸው ጋር ጤናን እና የጤና መረጃ ስርዓትን በቴክኖሎጂ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከኖርዌይ አቻቸው ኢንግቪልድ ጀርኮል ጋር ጤናን እና የጤና መረጃ ስርዓትን በቴክኖሎጂ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ካለው 75 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ጎንለጎን የሁለቱ አገራት ሚኒስትሮች በተለይም ጤናን እና የጤና መረጃ ስርዓትን በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ አቅም ገንቢ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የእውቀት ልውውጥ ዙሪያ ላይ መክረዋል።

በውይይቱ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፥ በኢትዮጵያ በግጭት የተጎዱ አከባቢዎችን ከመደገፍና ከማጠናከር አኳያ ኖርዌይ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል፡፡

የኖርዌይ የጤና ሚኒስትር ኢንግቪልድ ጀርኮል በበኩላቸው፥ አገራቸው በጤናው ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራትን አጠናክራ እንደምትቀጥል መግለፃቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.