Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ከሳዑዲ ዓረቢያ ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል ሳኡድ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከሳዑዲ ዓረቢያ ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል ሳኡድ ጋር ተወያዩ።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከሳዑዲ ዓረቢያው ንጉስ እና የሁለቱ ቅዱሳን መስጊዶች የበላይ ጠባቂ ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል ሳኡድ በሪያድ ከተማ አል ያማማ ቤተ መንግስት በነበራቸው ቆይታም የኢትዮጵያና የሳኡዲ አረቢያ ሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ እንዲሁም በጋራ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይቱ ላይም በሪያድ የኢፌዴሪ አምባሳደር አብዱልአዚዝ አህመድ፣ የሳኡዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈይሰል ቢን ፋርሃን ቢን አብዱላህ፣ ሚኒስትር ዴኤታና የካቢኔ አባል እንዲሁም የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ዶክተር ሙሳዓድ ቢን ሙሀመድ አል አይባን፣ እና የሳዑዲ አረቢያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አህመድ ቃጣን ተሳትፈዋል።

በኢፌዴሪ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ በሪያድ ቆይታው ከሳኡዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈይሰል ቢን ፋርሃን ቢን አብዱላህ ጋር መወያየቱንም በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.