Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ቴድርስ አድሃኖም መልካም ስራ ሰርተዋል- ቻይና

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዙሪያ መልካም ስራ መስራታቸውን ቻይና ገለፀች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በቻይና ብሄራዊ ኮንግረስ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ አበረታች ስራ መስራቱን አስታውቅዋል።

በተለይም የድርጅቱ ዋና ዳርዬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም መልካም ስራ ሰርተዋል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፥ የዓለም ሀገራትም ድርጅቱን ሊደግፉ ይገባል ብለዋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞም ጣቷን ወደ ቻይና እና የዓለም ጤና ድርጅት ለምትቀስረው አሜሪካም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንጊ ዪ፥ አሜሪካ ከዚህ ተግባሯ ብትቆጠብ መልካም ነው ብለዋል።

አሜሪካ ጣት በመቀሰር እና የተሳሳተ መረጃ በመዝራት ጊዜ ከማባከን ይልቅ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከቻይና ጋር ብትሰራ መልካም ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ reuters.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.