Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ በፓሪስ የኢፌዴሪ ሚሲዮን በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር የዩኔስኮ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ተመደቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በፓሪስ የኢፌዴሪ ሚሲዮን በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር የስራ ደረጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ምክትል ቋሚ መልእክተኛ ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል።

በዚህም መሰረት ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ከጥር 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በፓሪስ የኢፌዴሪ ሚሲዮን በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር የስራ ደረጃ የዩኔስኮ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው የሚሰሩ ይሆናል።

ዶክተር ጥላዬ አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ በሚሲዮኑ በመገኘት የተመደቡበትን ስራ በትጋትና በታማኝነት እንዲወጡ ጥሪ እንደቀረበላቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከውን ደብዳቤ ዋቢ በማድረግ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ባለፉት 34 ዓመታት በትምህርት ዘርፉ በተለያዩ ደረጃዎች ማለትም በፔዳጎጂ መምህርነት፣ በርዕሰ መምህርነት፣ በዞን አመራርነት፣ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትነት፣ በክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊነት፣ በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታነት እና በትምህርት ሚኒስትርነት አገልግለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.