Fana: At a Speed of Life!

ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በደቡብ ወሎ ግንባር ከአመራሮች እና ከሠራዊቱ ጋር ውይይት አድረጉ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ሀይሎች ጠ/ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በደቡብ ዕዝ ወሎ ግንባር ተገኝተው በሠራዊቱ የግዳጅ አፈጻፀም እና ባስመዘገባቸው ድሎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል ፡፡
በውይይቱም ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከውጪ ጠላቶቻችን ጋር በማበር እየሰራ ያለውን አሸባሪውን የህወሀት ሀይል ግብዓተ-መሬት ለማፋጠን እስካሁን የነበረውን ድል ከፍ ለማድረግ ጠንክሮ መስራት እንደምገባ ጀነራል ብርሀኑ አሳስበዋል ፡፡
አሸባሪው ኢትዮጵያን ለመበተን ጥረት ቢያደርግም አላማውን ማሳካት እንዳይችል በጀግናው ሰራዊታችን የተደመሰሰ መሆኑን ያወሱት ጠ/ኤታማዦር ሹሙ ፣ ለዚህ ድል መመዝገብ የሰራዊቱ አባላት ላደረጉት እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች እንደተናገሩት ፣ በነበረው የግዳጅ አፈጻፀምም አኩሪ ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡
ሠራዊታችን በአሁኑ ሰዓት በተሟላ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል ፡፡
ምንጭ:- ሀገር መከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.