Fana: At a Speed of Life!

ጀኔራል ሞተርስ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀኔራል ሞተርስ በኤሌክትሪክ የሚሰራ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪውን አስተዋወቀ።

አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ጀማሪ በሆነውና ከጀኔራል ሞተርስ ጋር በጥምረት የሚሰራው ክሩዝ አማካኝነት የተሰራ ነው።

ተሽከርካሪው መሪም ሆነ ፍሬንና ነዳጅ መስጫ የማይጠቀምና የመንገደኞች መቀመጫ ብቻ ያለው ነው ተብሏል።

ተሽከርካሪው ለሽያጭ ሳይሆን ለዕይታና ለልምድ ልውውጥ ብቻ የቀረበ መሆኑም ነው የተነገረው።

ሆንዳ ኩባንያ በአዲሱ ተሽከርካሪ ላይ ከጀኔራል ሞተርስ ጋር የባለቤትነት ድርሻ እንዳለው ተገልጿል።

ክሩዝ ከዚህ ቀደም በሳን ፍራንሲስኮ ሰው አልባ የንግድ ተሽከርካሪን ለመጀመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም ተሽከርካሪዎቹ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልጋቸዋል መባሉን ተከትሎ ማዘግየቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.