Fana: At a Speed of Life!

ጁንታውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጁንታውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተካሄደ፡፡

በዚህም በጅማ፣ በአጋሮ፣በደሌ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በጉጂ ዞን ጎሮ ዶላ ወረዳ፣በጂማ ዞን ጌራ ወረዳ እና በአርሲ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች የተካሄዱት ጁንታውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በሰላም ተጠናቀዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ “የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እንደግፋለን፣ ኦነግ ሸኔ እና ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ናቸው፣ በሕወሓት የጥፋት ኃይል ላይ እየተወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።

በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ÷ ሰላማዊ ሰልፉ ቡድኑ በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ እና ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከሰልፎቹ መጠናቀቅ በኋላም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለጀግናው የመከላከያ ሀይላችን የተለያዩ ድጋፎችን በአይነት እና በገንዘብ በመስጠት ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡
ከዚህ ባለፈም በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አስር የደም ባንኮችም “ደማችን ለመከላከያችን” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የሃገር መከላከያ ሰራዊት በቡድኑ ላይ እየወሰደ ያለውን ህግን የማስከበር ዘመቻ የሚደግፍ ነው ተብሏል፡፡
ሰልፈኞቹ የጁንታው የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈፀመውን ክህደት አውግዘዋል።
ነዋሪዎቹ ዛሬ በጅማ ስታዲየም በመገኘት ነው ህወሓት የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈፀመውን ጥቃት ያወገዙት።
በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የተፈፀመው ክህደት ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።
በመሆኑም መንግስት የጥፋት ሴራን አንግቦ መከላከያን በማጥቃት ሀገርን ለመበተን እየተንቀሳቀሰ ባለው የጅንታው ቡድን ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የሀገሪቷን ሰላም እንዲያስከብር ጠይቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ለመከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የገለጹት።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ትጃኒ ናስር ብርድና ቁር ሳይበግራቸው ህግን ለማስከበር ተጋድሎ እያደረጉ ላሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያላቸውን ክብርና አድናቆት ገልጸዋል።
የጅማ ከተማ መስተዳድርና ህዝብ ከመከላከያ ጎን በመሆን ለዘመቻው ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያርጉም ከንቲባው ተናግረዋል።
በሙክታር ጠሃ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.