Fana: At a Speed of Life!

ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ለ30 ሶማሊያውያን ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ለ30 የሶማሊያ ዜጋ ለሆኑ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል መስጠቱን አስታወቀ።
የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት ክልል አስተዳዳሪ አሲስ ላፍታግሪን ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፣ ከጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር በሺር እና ከሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም÷ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን እና ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
ዩኒቨርሲቲውም ለ30 የግዛቲቱ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል መስጠቱን በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.