Fana: At a Speed of Life!

ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ዝግጁ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ ላደረገው ትብብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጋና አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ ዝግጁ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ትብብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጋና አቅርባለች፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እንዲሁም የተለያዩ ሀጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጃንሜዳ የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የከተማ አስተዳደሩ ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል እንዲደርስ ቃል በገባው መሰረት እዚህ ደረጃ ደርሶ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ጃንሜዳን ለበዓሉ ማክበሪያ ዝግጁ ለማድረግ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ላደረጉት ትብብር በቤተክርስቲያኗ እና በህዝበ ክርስቲያኑ ስም አቡነ ማቲያስ ምስጋና አቅርበዋል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የጥምቀት በዓል የሁሉም ኢትዮጵያውያን በዓል የዓለም ቅርስ በመሆኑ ልንጠብቀው እና ልንንከባከበው ይገባል ብለዋል።

በዓሉ የኢትዮጵያዊነት ባህል እና እሴት የሚጎላበት በመሆኑ የአካባቢው ወጣቾች፣ የስፖርት ቤተሰቡ እና አርቲስቶች ተባብረው ለበዓሉ ትኩረት ሰጥተውት እየተሰራ ነው ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የዘንድሮው የጥምቀት በዓል እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸው ህዝበ ክርስቲያኑ ላሳየው ትዕግሥት እና ተሳትፎ ምክትል ከንቲባዋ አመስግነዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.