Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን በ2050 ከካርበን ነጻ ለመሆን ማቀዷን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺዴ ሱጋ በ2050 ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የካርበን ልቀት ዜሮ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገለጹ፡፡
ጃፓን በዓለም ላይ ካርበን ዳይኦክሳይድን ወደ ከባቢ አየር ከሚለቁ ሃገራት መካከል በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ከያዙ በኋላ የመጀመሪያውን የፖሊሲ ዕቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
ከዕቅዶቻቸው መካከል የሆነው በ2050 ከካርበን ነጻ የመሆን አላማ ዋነኛው ነው ተብሎለታል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአየር ንብረት መሻሻል ምላሽ መስጠት የኢኮኖሚ ጥያቄ ላይ እክል አይፈጥርም ብለዋል፡፡
ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ የአመለካከት ለውጥ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችም መወሰድ እንዳለባቸውም ነው የጠቀሱት፡፡
 
የሚወሰዱት እርምጃዎችም የኢንዱስትሪዎችን አወቃቀር ለአየር ንብረት በሚስማማ መልኩ እንዲቀርጹ ያደርጋቸዋል ነው ያሉት፡፡
 
የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር በበኩላቸው ከካርበን ልቀት ነጻ መሆን በራሱ አንዱ የኢኮኖሚ እድገት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
 
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግም ሃገራቸውን በ2060 ከካርበን ልቀት ነጻ ለማድረግ ዕቅድ መያዛቸው ተሰምቷል፡፡
 
 
ምንጭ፡- ሬውተርስ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.