Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን የኮሮና ቫይረስ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር ጥረት እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓን የኮሮና ቫይረስ በቶኪዮ 2020 የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር የተቻላትን ጥረት እንደምታደርግ ገለጸች።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሺንዞ አቤ ለዚህም ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የኦሊምፒክ ሚኒስትሩ ሰኢኮ ሃሺሞቶ በበኩላቸው አዘጋጆች በቀጣዩ ሐምሌ ወር የሚካሄደውን የኦሊምፒክ ውድድር የመሰረዝ ሃሳብ እንደሌላቸው አስረድተዋል።

በኮሮና ቫይረስ እስካሁን 361 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተነግሯል።

በጃፓን 20 ሰዎች ላይ ቫይረሱ የተገኘ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 17ቱ ከቻይና የመጡ አልያም ቻይናውያን ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል።

ቫይረሱ ከቻይና ውጭ ባሉ ሃገራት መሰከቱን ሪፖርት የሚያደርጉ ሀገራት ቁጥርም እያደገ መምጣቱ ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.