Fana: At a Speed of Life!

ጆን ማጉፉሊ ለሁለተኛ ጊዜ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ማሸነፋቸው ተሰማ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ተቀናቃኛቸው ቱንዱ ሊሱን በሰፊ የድምጽ ብልጫ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በተደረገ የድምጽ ቆጠራ ማጉፉሊ 84 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ ቱንዱ ሊሱ ደግሞ 13 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል ነው የተባለው፡፡

ውጤቱን ተከትሎ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ደስታቸውን ሲገልጹ ተቀናቃኙ ሊሱ ግን የምርጫ ውጤቱ ተጭበርብሯል በሚል ወንጅለዋል፡፡

የእርሳቸው ፓርቲ ተወካዮችም ባለፈው ረቡዕ በተደረገው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንም ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ኮሚሽኑ በበኩሉ ውንጀላውን አስተባብሏል፡፡

የጆን ማጉፉሊው ሲ ሲ ኤም ፓርቲ ታንዛኒያን ከነጻነት በኋላ እያስተዳደራት ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.