Fana: At a Speed of Life!

ጆ ባይደን ለዓየር ንብረት ለውጥ እና ለጤና የቀረበው ረቂቅ ላይ ፈረሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዓየር ንብረት ለውጥ እና ጤና ጥበቃ የተጠየቀውን የ700 ቢሊየን ዶላር ህግ ሥራ ላይ እንዲውል በፊርማቸው ማጽደቃቸው ተገለጸ፡፡

ህጉ በዋናነት ባለሐብቶች በሚከፍሉት የገቢ ግብር ላይ ጭማሪ በመጣል ወጪውን እንደሚያሟላ ተመላክቷል፡፡

ይህ ህግ ሲተገበር በሚወሰዱ እርምጃዎች በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶች ዋጋ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ቅናሽ እንደሚኖር ተሥፋ ተጥሎበታል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ፊርማ ሕዳር ወር ላይ በሚካሄደው የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ለዴሞክራቶች ድጋፍ ሊያስገኝላቸው እንደሚችልም እየተነገረ ነው።

ታዛቢዎቹም የፕሬዚዳንቱ ውሳኔ በአጋማሽ ወር ምርጫው በህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የዴሞክራቶቹ የበላይነት እንዲያበቃ ሊያደርግ ይችላል እያሉ ነው።

ባይደን በፈረሙት ረቂቅ ህግ ላይ የዓየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የሚያስችል 375 ቢሊየን ዶላር መበጀቱ ተጠቁሟል፡፡

በጀቱ በዓየር ንብረት ለውጥ ተመራማሪዎች በአወንታዊነት ተወስዷልም ነው የተባለው፡፡

የዘርፍ ባለሙያዎችም በቀጣይ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመግታት በቂ ባይሆንም አወንታዊ ለውጥ ይኖረዋል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎችም በጀቱ በቀጣይ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት በቂ ባይሆንም አወንታዊ ለውጥ ይኖረዋል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአሁኑ ህግ አሜሪካ ወደ ከባቢ አየር የምትለቀው የበካይ ጋዝ መጠን በፈረንጆቹ 2030 በ44 በመቶ ለመቀነስ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

አዲሱ ህግ ትላልቅ ኩባንያዎች ወደ ከባቢ አየር የሚለቁትን በካይ ጋዝ እንዲቀንሱ ግዴታ የሚጥል ግን አይደለም።

ከዚያ ይልቅ ኩባንያዎቹ ፊታቸውን ወደ አረንጓዴ ልማት (ታዳሽ ሃይል) እንዲያዞሩ ማድረግን የሚያበረታታ ሲሆን፥ ይህን ማድረግ ከቻሉም የግብር እፎይታ ያስገኝላቸዋል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ለሚገዙ ሰዎች ቅናሽ ማድረግ፣ ብድር ማመቻቸት እንዲሁም በተራዘመ ክፍያ ግዢ እንዲፈጽሙ እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው።

በጤናው ዘርፍም እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆናቸው አሜሪካውያን የታዘዙላቸውን መድኃኒቶች በቅናሽ ዋጋ እንዲያገኙ፥ መንግስት በጤና መድህን በኩል ከመድኃኒት አቅራቢዎች ጋር እንዲደራደር የሚያስችለው ነው።

በባይደን የተፈረመው አዲሱ ህግ ትላልቅ ኮርፖሬሽኖች የሚከፍሉት ዝቅተኛ የግብር መጠን 15 በመቶ እንዲሆን የሚያዝ ሲሆን፥ ከ400 ሺህ ዶላር በታች ዓመታዊ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ግን የግብር ጭማሪ አያደርግም ተብሏል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.