Fana: At a Speed of Life!

ጆ ባይደን የ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማገገሚያ ማዕቀፍ ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማገገሚያ ማዕቀፍ ይፋ አደረጉ፡፡

በፕሬዚዳንቱ ይፋ የሆነው ይህ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ እቅድ በኮሮና ቫይረስ የተጎዳውን የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመታደግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከባይደን እቅድ ውስጥም 415 ቢሊየን ዶላሩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የሚውል ሲሆን፥ 440 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ አነስተኛና ጥቃቅን የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማነቃቃት የሚውል ነው፡፡

ከዚህ ውስጥ 20 ቢሊየን ዶላሩ ለክትባት ይውላል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡

ባይደን የቫይረሱን የምርመራ ሂደት ማስፋትና ትምህርት ቤቶችን በፀደይ ወራት ዳግም መክፈትንም ሌሊቱን ይፋ በደረጉት የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅዳቸው ውስጥ አካተውታል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥም ለበርካታ የጤና ባለሙያዎች የስራ እድልን ይፈጥራሉ ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ባለፈም የእርሳቸው አስተዳደር በመጀመሪያዎቹ 100 የስራ ቀናት ውስጥ 100 ሚሊየን የስራ እድሎችን ለመፍጠር ስለማለሙም ይፋ አድርጓል፡፡

የእርሳቸው እቅድ በኮንግረሱ ይሁንታን ካገኘም አሜሪካውያን 1 ሺህ 400 ዶላር በቀጥታ እንደዲያገኙ ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡

አሁን ላይ በአሜሪካ ወደ 11 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ስራ አጥ ሲሆኑ አዲሱን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ለስራ አጦች ይለቀቅ የነበረው ሳምንታዊ የገንዘብ መጠንም ከፍ ይላል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.