Fana: At a Speed of Life!

ገናን በላሊበላ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ገናን በላሊበላ ጥምቀትን በጎንደር በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
 
የቢሮው ሃላፊ አቶ ጣሂር ሙሐመድ ዛሬ በላሊበላ ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በመግለጫቸው የህወሓት የሽብር ቡድን በቆየባቸው ጊዜያት የላሊበላ እና አካባቢውን ቅርሶች አባቶች መስዋዕትነት በመክፈል ጠብቀው በሰላም ማቆየታቸውን ተናግረዋል።
 
በአሁኑ ሰዓት የተዳከመውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማነቃቃት እንዲሁም በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ የተጎዳውን ማህበረሰብ ለመደገፍ የዘንድሮውን የገና በዓል በልዩ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
 
አቶ ጣሂር በህወሓት የሽብር ቡድን የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለማልማት በተለይም የትራንስፖርት፣ የውሃ እና መብራት አገልግሎት በአጭር ጊዜ እንዲሟሉ የሚያስፈልጉ ነገሮች ተለይተዋል ብለዋል።
 
ሁሉም ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለበዓሉ ሲመጡ ሃይማኖታዊ በረከቱን ከመቋደስ ባለፈ ህዝቡን ከጎንህ አለን እንዲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
 
በዚህ ሂደት ከፌደራል ጀምሮ የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
 
አያይዘውም በዓይነቱ ልዩ የሆነውን የገና በዓል በድምቀት እናከብራለን ብለዋል።
 
በምንይችል አዘዘው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.