Fana: At a Speed of Life!

ጉምሩክ ኮሚሽን ከኮንሶ ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች 24 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከኮንሶ ዞን በተፈጥሯዊ እና በሰው ሠራሽ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች 24 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በኮንሶ ተገኝተው አስረክበዋል።
የተደረገው ድጋፍ ቤት መሥሪያ ቆርቆሮ፣ ምስማር እንዲሁም የምግብ ዘይት፣ ስኳር እና የተለያዩ ልብሶች እንደሆነ ተገልጿል።
ድጋፉ በኮንሶ ዞን በተፈጥሯዊ ምክንያት እና በሰው ሠራሽ ግጭቶች ለተፈናቀሉ 80 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሚደርስ ይሆናል ነው የተባለው።
ኮሚሽኑ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የተለያዩ ዜጎች 4 ቢሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን ኢቢሲ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.