Fana: At a Speed of Life!

ጉግል አዲሱን የግላዊነት ፖሊሲ ተግባራዊ የሚያደርግበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎግል የሶስተኛ ወገን አጠቃቀምን የሚገድብ አዲስ የግላዊነት ማስጠበቂያ ፖሊሲ የሚተገበርበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ።

ተቋማት በበይነ መረብ ላይ እየጨመረ የመጣውን ጥቃት ተከትሎ የግላዊነት ጥበቃ ደህንነታቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያደርግ ግፊት እየጨመረ ነው።

ለዚህ ደግሞ በሶስተኛ ወገን የተጠቃሚዎችን የበይነ መረብ እንቅስቃሴ መከታተል የሚያስችሉት መሳሪያዎች (ኩኪዎች) ጋር በተያያዘ ያለው አጠቃቀም አናሳ መሆኑ ይነገራል።

ጎግልም በሶስተኛ ወገን አጠቃቀምን የሚገድብ አዲስ የግላዊነት ማስጠበቂያ ፖሊሲ የሚተገበርበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

አዲሱ ፖሊሲ ፕራይቬሲ ሳንድቦክስ የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን፥ የሶስተኛ ወገን ማስታወቂያ አሰራጮች የተጠቃሚዎችን መረጃ በፈለጉት ጊዜ ሳይሆን በጎግል አማካኝነት እንዲያገኙ የሚያደርጋቸው ነው።

ይህ መሆኑ ደግሞ ጎግል በዲጂታል ማስታወቂያ ገበያው ያለውን ተደራሽነት የበለጠ ያሰፋለታል እየተባለ ነው።

ኩኪዎች የዲጂታል ማስታወቂያ ባለሙያዎች የተጠቃሚዎችን እንቅስቃሴ ማዕከል ተንተርሰው ማስታወቂያ እንዲሰሩ ይረዷቸዋል።

ኩባንያዎች በበይነ መረብ ላይ የግለሰቦችን እንቅስቃሴ ለማወቅ የመረጃ ማፈላለጊያዎች ላይ የተከማቹ መረጃዎችን ይጠቀማሉ።

በዚህም የጎበኟቸውን ድረ ገጾች ጨምሮ በዲጅታል ማስታወቂያ የተደረጉ የግብይት እንቅስቃሴዎችን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፥ ማስታወቂያ ሰሪዎችም ተጠቃሚወችን መሰረት ያደረገ መረጃ እንዲለቁ ያግዛቸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.