Fana: At a Speed of Life!

ጊኒ የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጊኒ በኢቦላ ወረርሽኝ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ቫይረሱ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች።

በጊኒ ደቡብ ምስራቅ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ለህልፈት ከተዳረጉት ሰዎች ባሻገር አራት ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሯል።

በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ጎዋኬ በአንድ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተሳተፉ 7 ሰዎች የማስመለስ፣ የመድማት እና ማስቀመጥ  እንዳጋጠማቸው ተጠቁሟል።

የኢቦላ ቫይረስ የተገኘባቸው እነዚህ ሰዎች አሁን ላይ በለይቶ ማቆያ እንደሚገኙ የጊኒ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትሩ ሬሜይ ላማህ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በኢቦላ ተከሰተው ሞት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በጊኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከስቶ ከፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 የቆየው የኢቦላ ወረርሽኝ በምዕራብ አፍሪካ የ11 ሺህ 300 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ በተለይ ኢቦላ በተከሰተበት አካባቢ የምርመራ እና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅትም በጊኒ የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱ እንዳሳሰበው መግለጹም ይታወሳል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.