Fana: At a Speed of Life!

ጊዜያዊ የመራጮች ምዝገባ መረጃ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)እስካሁን ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከ36 ሚሊየን 245 ሺህ በላይ ሰዎች ተመዝግዋል፡፡

በዚህም በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ማለትም በአዲስ አበባ 1ነጥብ451 ሺህ 790ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 177ሺህ 519 ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡

እንዲሁም በክልሎች፤ አፋር 1ነጥብ 714 ሺህ 989፣ አማራ 5ሚሊየን 966 ሺህ 662፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 174 ሺህ 768፣ ጋምቤላ 326ሺህ 648፣ ኦሮምያ 15ሚሊየን 938ሺህ 213፣ ሃረሪ 135 ሺህ 584፣ ደቡብ 4ሚሊየን 854ሺህ 588፣ ሲዳማ 1ሚሊየን 540 ሺህ 889 እና በሶማሊ 3 ሚሊየን 963 ሺህ 794 ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡

በአጠቃላይ በመላው አገሪቱ ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለመምረጥ የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር 36 ሚሊየን 245ሺህ 444 ሆኗል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.