Fana: At a Speed of Life!

ጋቦን ከካርበን ሽያጭ 275 ሚሊየን ዩሮ ለማግኘት አቀደች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋቦን ጥቅጥቅ ደኖቿን ለካርበን ገበያ በማቅረብ 275 ሚሊየን ዩሮ ገቢ ለማግኘት አቅጇለሁ አለች፡፡

ሀገሪቷ ገቢውን ለማሳካት ያቀደችው ሕዳር ወር ላይ በካይሮ ከሚካሄደው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ወዲህ ነውም ተብሏል፡፡

በዚህ ዓመት በሩዋንዳ በተካሄደው የጋራ ብልጽግና ሀገራት ጉባዔ ላይም ጋቦን ከደን ሽፋኗ በዘላቂነት ገቢ ማመንጨት እንደምትፈልግ እና የደን ልማት መርሐ-ግብሯንም እንደምታጠናክር የሀገሪቷ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሊ ዋይት ጠቁመዋል፡፡

ጋቦን ከካርበን ሽያጭ ተጠቃሚ የምትሆነው በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ሥምምነት ማዕቀፍ መሠረት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጋቦን የደን ጭፍጨፋ እንዳይባባስ ላደረገችው ጥረት የገንዘብ ድጋፍ ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ ተነግሯል።

ሀገሪቷ በፈረንጆቹ 2019 በተመድ ከሚደገፈው “የመካከለኛው አፍሪካ የደን ኢኒሼቲቭ “17 ሚሊየን ዶላር ማግኘቷም ይታወሳል፡፡

ኢኒሼቲቩ ÷ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ ለሚሰሩ ሀገራት በድምሩ 150 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አድርጓልም ነው የተባለው፡፡

ጋቦን ከደቡብ አሜሪካዋ ሱሪናም ቀጥሎ በደን ሽፋን ከዓለም ሁለተኛዋ ሀገር ስትሆን በቀጣይ በካርበን ሽያጭ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ከሚኖራቸው ሀገራት ተርታ እንደምትሰለፍ ብሉምበርግ እና ዘ አፍሪካ ሪፖርት ዘግበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.