Fana: At a Speed of Life!

ግልገል ጊቤ II የኃይል ማመንጫ ቀልጣፋ የጥገና አሰራርን ለመፍጠር የዲጂታል መፍትሄዎች ሊተገብር ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግልገል ጊቤ II የውሃ ኃይል ማመንጫ ይበልጥ ቀልጣፋ የጥገና እቅድ ለመተግበር የሚያስችለውን የቮይዝ ሃይድሮ ዲጂታል መፍትሄዎችን ሊተገብር ነው ፡፡

ከቮይዝ ሀይድሮ ጋር በመተባበር በሚተገበረው ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀልጣፋ የጥገና እቅድን ማከናወን የሚያስችለው ይሆናል።

በዚሁ መሰረት የቮይዝ ሀይድሮ ዲጂታል መፍትሔዎች በኢትዮጵያ የግልገል ጊቤ II የውሃ ኃይል ማመንጫ ላይ ይተገበራሉ።

ባለፈው ዓመት በቮይዝ እና የኢትዮጵያ ኤሌክሪክ ኃይል መካከል ከተፈረሙ ሁለገብ የሁለት ዓመት አገልግሎት እና የጥገና ውሎች ባለፈ በአሁኑ የዲጂታል መፍትሄ “የኦንኬር፣ አሴት እና ኦንኮል ቪዲዮ” አገልግሎቶች ተካተውበታል ፡፡

የቀድሞው ውል የጥገና ስርዓቶችን ማመቻቸት እና የዕለት ተዕለት ሥራዎች ድጋፍን ያካተተ ሲሆን ስራዎቹ በቦታው ላይ በሚገኙ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች የሚተገበሩ መሆናቸውም ነው የተመላከተው።

በዚህም ውል በሃይል ማመንጫው ውስጥ ያለው ሥራ በአሁን ወቅት ዘመናዊና ዲጂታል መፍትሄዎችን በማስቀመጥ በአዲሱ ውል የበለጠ እንደሚሻሻልም ነው የተነገረው።

ከዚያም ባለፈ እየተጫኑ ያሉት የዲጅታል ትግበራዎች ለጥገና እቅድ እና አፈፃፀም እንዲሁም ለሪፖርት እና መለዋወጫ አያያዝ አገልግሎት ሊውሉ ይችላሉ ተብሏል ፡፡

በተጨማሪም የዲጂታል መፍትሄዎች ትግበራው ኦንኬር፣ አሴት ፣ ጥገና እና የአሰራር ወጪዎችን መቀነስ ያስችላል።

ቮይዝ ሀይድሮ የእውቀት ሽግግርን ለማመቻቸት እና ማሻሻያዎቹን ዘላቂ ለማድረግ የመለዋወጫ እና የሰራተኞች ስልጠና ይሰጣል መባሉን የዓለም አቀፋዊ የውሃ ሃይል እና የግድብ ግንባታ አስታውቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.