Fana: At a Speed of Life!

ግብርን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ አመታዊ  ግብሩን በማሳወቅ ግብሩን እንዲከፍል የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳሰበ።

ቢሮው ዛሬ በከተማዋ ካሉ ግብር ከፋይ ተወካይ ነጋዴዎች ጋር የ2012 የግብር ማሳወቂያ ጊዜን በተመለከተ ምክክር አካሂዷል።

በምክከር መድረኩ ላይ የቢሮው ሃላፊ አቶ ሺሰማው ገ/ስላሴ የኮቪድ 19ን በመከላከል ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብሩን በወቅቱ እንዲከፍል ቅድመ ዝግጀት ተደርጓል ብለዋል።

በቀጣይ 4 ወራት ውስጥ ማለትም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 2013 ድረስ በየደረጃው ያሉ ግብር ከፋዮች አመታዊ ግብራቸውን በማሳወቅ የሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.