Fana: At a Speed of Life!

ግብጽ ከአስዋን ግድብ የምታባክነው ውሃ የህዳሴ ግድብን በተያዘለት ጊዜ መሙላት የሚያስችል ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ግብጽ ከአስዋን ግድብ የምታባክነው ውሃ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውሃ መሙላት የሚያስችል መሆኑን የምስራቅ ናይል ቴክኒካል አህጉራዊ ጽህፈት ቤት ዋና ስራአስኪያጅ ገለጹ።

የምስራቅ ናይል ቴክኒካል አህጉራዊ ጽህፈት ቤት ዋና ስራአስኪያጅና የድርድሩ ተሳታፊ አቶ ፈቅ አህመድ ነጋሽ ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ የምትገነባው ህዝቦቿን ከድህነትና ከጨለማ ለማውጣት መሆኑ ለማንም ግልጽ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የግድቡ ግንባታ በራሷ የተፈጥሮ ሃብት፣ በራሷ ጉልበትና በራሷ ገንዘብ በሌሎች ላይ ጉልህ ጉዳት በማያደርስ መልኩ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ሆኖም ለአባይ ወንዝ ምንም አስተዋጽኦ የሌላት ነገር ግን የወንዙ ከፍተኛ ተጠቃሚ የሆነችው ግብጽ በግድቡ ላይ መርህ የሌለው ተቃውሞ እያሰማች መሆኑን ማስረዳታቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ለአባይ ወንዝ 86 በመቶን የምታበረክት ብትሆንም በጋራ የመጠቀምን መርህ ተከትላ ጉልህ ጉዳት በማያስከትል መልኩ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመገንባት ለውሃ ሙሌት በመዘጋጀት ላይ ትገኛለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.