Fana: At a Speed of Life!

ግንባታው የዘገየው ሃገር አቀፍ የልዩ ተሰጥኦ ማስተማሪያና ማበልጸጊያ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡራዩ ከተማ እየተገነባ ያለው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሃገር አቀፍ የልዩ ተሰጥኦ ማስተማሪያና ማበልጸጊያ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 91 በመቶ መድረሱ ተረጋገጠ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ልዑካን በቡራዩ ከተማ እየተገነባ ያለውን የልዩ ተሰጥኦ ማዕከልና ወደ ማዕከሉ የሚያስገባውን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ጎብኝቷል።

የፕሮጀክቱ ፊዚካዊ አፈጻጸም ከሦስት ወር በፊት ከነበረበት የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይሁን እንጅ ከሚጠበቀው አኳያ በታቀደለት ጊዜ መጠናቀቅ አልቻለም ተብሏል።

የግንባታ ሂደቱ በሩብ ዓመቱ ከነበረበት የ80 በመቶ አሁን ላይ ወደ 91 በመቶ እድገት ማሳየቱም ነው የተጠቆመው።

የቡራዩ ከተማ አስተዳደርና ሕዝብ ከፕሮጀክቱ ጅማሮ እስካሁን ላሳዩት ያልተቋረጠ ድጋፍና ተጠናክሮ ለቀጠለው ትብብር ከሚኒስቴሩ ልዑካን አድናቆትና ምስጋና ተችሯቸዋል።

የፕሮጀክቱ አካል የሆነውና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተገነባ ያለው የ1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ግንባታ ለከተማዋ አዲስ ትሩፋትና ለነዋሪው ማህበራዊ ኑሮ መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.