Fana: At a Speed of Life!

ጠላት ተሸንፏል፤ ቀጣይ ስራችን ጠላትን መበተን እና መደምሰስ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠላት ተሸንፏል፤ ቀጣይ ስራችን ጠላትን መበተን እና መደምሰስ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

አሁን የገጠመን ጠላት የሚዘርፍ፣ የሚሰርቅ፣ የሚደፍር፣ለሴቶች ክብር የሌለው እና እራሱን አዋርዶ እኛንም ማዋረድ የሚፈልግ ነው ብለዋል፡፡

ይህ ሃይል ሳያቅድና ሳያልም በእውር ድንብር ወደ ጦርነት ገብቷል ፤በእውር ድንብር ግን አይወጣም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በጋሸና የምናደርገው የማጥቃት ስራ ወሳኝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ ጠላት ሳያስብ የወሰነው ውሳኔ ካመጣበት ኪሳራ ትምህርት የሚያገኝበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ይህን ለማድረግም ዕቅድ አውጥተን ጨርሰናል፤ ሰራዊታችንም ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

መቼ እና እንዴት የሚለው ከወሰንን በኋላም ጋሸና ላይ በድል የምንገናኝበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ነው ያሉት፡፡

የትግራይ ወጣት እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የትግራይ ወጣት መሸነፉን በመረዳት ፤ዕቅድ በሌለውና መዳረሻው በማይታወቅ ጉዞ ድል እንደሌለ አውቆ እጁን ለሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለልዩ ሃይሎች እንዲሁም ለሚሊሻ አባላት እንዲሰጥ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ይህን ማድረግ ካልቻለም ሰሞኑን ባየው በመከላከያ ሰራዊት ብርቱ ክንድ የመደመሰሱ ሁኔታ እንደሚቀጥልም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በሌላ በኩል የትግራይ እናቶችም ልጆቻቸው የት እየደረሱ እንደሆነ ሊጠይቁ ይገባል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግንባር ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

እኛ ጦርነት አንፈልግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ ሰላም ፣የሃገር አንድነትን ነው የምንፈልገው ነገር ግን ሃገር እናዋርዳለን፤ እናፈርሳለን ብሎ የገባውን ሃይል እናፈርሳለን ፣እንደመስሳለን ፣የሃገራችንን ክብርም እናስጠብቃለን ብለዋል፡፡

ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ነው ያሉት፡፡

ለዚህም ሰራዊቱ ያለው ዝግጁነት አመርቂ በመሆኑ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ይህንን ግንባር ጨርሰን ወደ ሌሎች ግንባር እንዞራን ብለዋል፡፡

ህዝቡም የሚያደርገውን ደጀንነት አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

 

በፌቨን ቢሻው

 

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.