Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ዛፍ በደጃፍ” በሚል መርሃ ግብር ከቤተሰቦቻቸው ጋር ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ዛሬ ችግኝ ተክለዋል።

የ2012 የአረንጓዴ አሻራ በትናንትናው እለት በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

ይህንንም ተከትሎ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ “ዛፍ በደጃፍ” በሚል መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከባለቤታቸው ከቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እና ከልጆቻቸው ጋር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው ችግኞቹን የተከሉት።

የኮቪድ-19 ወረርሽን መከላከል እንዲቻልም ህብረተሰቡ በ”ዛፍ በደጃፍ” መርሃ ግብር በመሳተፍ ችግኞቹን በግቢው እና በመንደሩ በመትከል እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከል ችለዋል።

ትናንት በይፋ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመላው ሀገሪቱ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ ዝግጅት ሲደረግ ተቆይቷል።

 

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.