Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሶማሌ ክልል የተተገበረውን የመሰረተ ልማት አውታር አደነቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሌ ክልል በአጭር ጊዜ ተግባራዊ የተደረገውን ሰፊ የመሰረተ ልማት አውታር ግንባታ አድንቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ÷ በዘመናዊ መልኩ ዕድሳት የተደረገለትን የሶማሌ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ጽኅፈት ቤት ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በክልሉ በነበራቸው መርሐ-ግብር በፋፈን ዞን በክላስተር የለማውን የስንዴ ማሳ መጎብኘታቸውም ተመላክቷል፡፡
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር ÷ ባለፉት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ቢበዛ 10 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኝ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በዚህ ዓመት ግን የክልሉ መንግስት ምርቱን ወደ 28 ሚሊየን ኩንታል ለማሳደግ ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መግለጻቸውን ከሶማሌ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.